በቀጣይ ሳምንታት የሚከበሩ የመስቀል እና ኢሬቻ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በቀጣይ ሳምንታት የሚከበሩ የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብረዉ እንዲያልፍ የወጣቶች ሚና

በቀጣይ ሳምንታት የሚከበሩ የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብረዉ እንዲያልፍ የወጣቶች ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ።

*

መስከረም 11/2017

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በመስከረም ወራት የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት ሐይማኖታዊና ባህላዊ ትዉፊታቸዉን ጠብቀዉ በሠላም እንዲከበሩ ብሎም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ይዘቱን ብቻ በመከተል በዓሉን ታድመዉ በሠላም እንዲመለሱ፤በየደረጃው ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የምክክር እና የዉይይት መድረክ መካሄዱ እንደቀጠለ ነዉ።

በዛሬዉ እለትም ቢሮዉ በቀጣይ ተከታታይ ሳምንታት የሚካሄዱ የመስቀልና ኢሬቻ የአደባባይ ክብረ በዓላትን አስመልክቶ ከ11ዱም ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የወጣት ማህበር አባላት ጋር የዉይይትና የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ወጣት በረከት ቢርቢርሳ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት እንደተናገሩት፤ ሀገር ላለችበት የእድገትና ብልጽግና ጉዞ የወጣቱ ሚና ጉልህ እንደሆነ ገልጸዉ፤ ሀገራችን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን አሳክታ በማንሰራራት ላይ ያለችበት ወቅት በመሆኑ በቀጣይ ሳምንታት የሚከበሩ የሰላምና የፍቅር ተምሳሌት የሆኑ እና በዩኒስኮም ጭምሮ የተመዘገቡት የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ቱውፊቱንና ዕሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር የወጣቱ ሚና ጉልህ አስተዋጽኦ ስላለዉ የማህበሩ አባላት በሙሉ ከዚህ ቀደም ሲያደርጉ እንደነበረዉ ሁሉ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት ሁሉ ወጣቶች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል ።

የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ሚደክሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/የቢሮ ሀላፊ በበኩላቸዉ፤ በበዓላቱ አከባበር ላይ ህብረ ብሄራዊነታችንን በማረጋገጥ እህትና ወንድማማችነትን በማጎልበት ሰፊ ስራ መስራት መቻል እንደሚገባ ጠቅሰዉ፤ አንዳንድ ፀረ ሰላም ኃይሎች በስውርም ይሁን በግልጽ የከተማዉን ሰላምና የህብረ ብሄራዊነታችን መገለጫ የሆኑ በዓሎቻችን በሠላም እንዳናከብር ፀጥታ የሚረብሹ አካላት እንዳይኖሩ ከወጣቱ ትልቅ ስራ ይጠበቃል በማለት ገልጸዋል።አቶ ሚደክሳ አያይዘዉም የዩኔስኮ ቅርስ በሆኑና ለመሆን ሂደት ላይ ባሉ በዓላት ከመላው አለም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ቱሪስትና የሚዲያ ሰዎች የሚታደሙበት በመሆኑ ለሀገራችን እድገት ትልቅ ሚና የሚጫወት ስለሆነ በቀጣይ ቀሪ ጊዜያት በተወያየነዉ ልክ ስራዎችን መስራት ከወጣቱ ይጠበቃል ሲሉ ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ አቶ ሚደክሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ፤ ወጣት በረከት ቢርቢርሳ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት፤ ወ/ሮ ፎሊ ንጉሴ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የ11ዱም ክፍለ ከተሞች የወጣት ማህበር አደረጃጀት ሰብሳቢዎችና ከ1ሺህ በላይ የመድረኩ ተሳታፊ ወጣቶች የተገኙ ሲሆን ከበዓላቱ ጋር ተያይዞ በቢሮዉ ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ አማካኝነት የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎበታል።

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች እንደገለጹት ከሆነ የወጣት ማህበሩ ያለምንም ልዩነት በሰላም ወዳድነት፣ በአብሮ መኖር፣ በመረዳዳትና በእንግዳ ተቀባይነቱ የሚታወቅ በመሆኑ በዚህ አመትም ያንኑ መርህ በማስቀጠል የመስቀል ደመራና የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓላት የሁሉም ኢትዮጵያዊ በዓላት በመሆናቸው በሰላም ተከብረው ይጠናቀቁ ዘንድ የበኩላቸችንን ድርሻ በኃላፊነት እንወጣለን ሲሉም ተደምጠዋል።

በመጨረሻም በቀረበው የመወያያ ሰነድ ዙሪያ ወጣቶች ባነሱት ሀሳብና አስተያየቶች ላይ በአቶ ሚደክሳ እና ወጣት በረከት ምላሽ ተሰጥቶ፤ ከበዓላቱ ጋር ተያይዞ በቀሪ ጊዜያት መከናወን ያለባቸዉን ዝርዝር ተግባራት አቅጣጫ ሁለቱም ኃላፊዎች በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።