በ2018 በጀት አመት የተከለሰ መሪ እቅድ
የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ በ2018 በጀት አመት የተከለሰ መሪ እቅድ ላይ እና በ90 ቀናት እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ።
መስከረም 06/2018 (አዲስ አበባ)
**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የ2018 በጀት አመት የተከለሰ መሪ እቅድ እና የ90 ቀናት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ የዘርፉ አስተባባሪዎች፤ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
መድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ፤
እንኳን ለ2018 ዓ.ም እንዲሁም አንድነታችንን የሚያሳይ ታሪክ በመስራት ለትውልድ ያስተላለፍነውን የኢትዮጵያ የማንሰራራትና የከፍታ ዘመን አደረሳችሁ በማለት ይህንን ስኬት ወደ ዘርፍ በማምጣት እስከ ወረዳ ያለን የዘርፉ ባለሙያዎች የተሰጠንን ሃላፊነት በታማኝነትና በትጋት መወጣት እንደሚገባና በዚህ ወር የሚካሄዱ የአደባባይ ክብረ በአላት ባህላዊ እሴቶችና ሃይማኖታዊ ቱፊታቸውን ጠብቀው እንዲያልፉ ለማድረግ ሁላችንም በመተባበር በጥብቅ ዲሲፕሊን መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
አቶ ብርሃኑ አክለውም ይህ እቅድ በዚህ በአዲሱ በጀት ዓመት የምንመራበት በመሆኑ ተግባራችንን ቆጥረን ወስደን ማስፈፀም እንደሚገባ ገልፀው፤ ባለፉት 90 ቀናት በተሰሩት ስራዎች ውስጥ ያሉት ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል ክፍተቶችን ደግሞ በማስተካከል መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ደይሬክተር አቶ ሙሉቀን እንየው የ2018 በጀት አመት እቅድን ባቀረቡበት ወቅት፤ ህዝብ ለህዝብ ትስስር መጠናከር፣ በሰላም ግንባታ ስራ ላይ ከተቋማት ጋር ምርጥ ተሞክሮ መውሰድ፣ አገራዊ አንድነትና ማህበራዊ ትስስር የሚያጎለብት ስልጠና መስጠት፣ የሃይማኖትና እምነት ተቋማት በሰላምና በልማት ጉዳዮች ላይ ተሳትፎን ማሳደግ እንደሚገባ አብራርተው የ90 ቀናት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና ካስኬዲንግ አቅርበዋል።
በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ለቀረበው ጥያቄና አስተያየት በአቶ ብርሃኑ ረታ ምላሽ ተሰጥቶ በወረደው ካስኬድ ላይ ከ11ዱ ክፍለከተማ የዘርፉ ስራሂደቶች ጋር የመፈራረም ስነስርአት ተከናውኗል።