የ2017በጀት ዓመት የቅንጅት ሥራዎች አፈፃፀም...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የ2017በጀት ዓመት የቅንጅት ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማ

በተሰሩ ቅንጅታዊ ስራዎች ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ከማድረግ ባሻገር አስተማማኝ ሰላም ማስፈን ተችሏል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

ሰኔ 28/2017ዓ/ም( አዲስ አበባ)

*******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በበጀት ዓመቱ አብሮ በቅንጅት ለመስራት የትስስር ሰነድ ከተፈራረማቸው ተቋማት ጋር የ2017በጀት ዓመት የቅንጅት ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

በውይይቱ መግቢያ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ሰላምና ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ አመራሩ፣ ህብረተሰቡና የፀጥታ አካሉ አቅም የሆነው በትስስር እና በቅንጅታ በሰራቸው ሥራዎች አስተማማኝ ሰላምን ማስፈን የተቻለ መሆኑን ገልፀዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ አክለውም ህብረተሰቡ የሰላም ባለቤት እየሆነ የመጣ መሆኑን ጠቅሰው የፀጥታ ስጋቶችን ከማስቆምና የወንጀል ድርጊቶችን ከመቀነስ ባሻገር በከተማዋ ላይ የአደባባይ በዓላት ሲከበሩ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመሆን በዓላቱ ቱውፊታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ከማድረግ አኳያ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች የተገኙ መሆኑንም ገልፀዋል።

በተሰሩ ቅንጅታዊ ስራዎች ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ፣ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ቦታዎቾ ከስጋት ነጻ የማውጣት ፣ህገ-ወጥ መሳሪያና የገንዘብ ዝውውርን መከላከል፣ የፀረ ሰላም ሀይሎች ክትትል በማድረግ እርምጃ መውሰድ፣የህግ አስከባሪ አካላትን በጥራት በመመልመል አቅም የመገንባት፣ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የማወያየትና ሌሎች ተግባሮችም መከናወናቸውን በሪፖርቱ ቀርቧል።

ቢሮው በበጀት አመቱ ከ28 ተቋማት ጋር አብሮ ለመሥራት የትስስር ሰነድ መፈራረም ብቻ ሳይሆን ሥራውን ለመሥራት አቅደው ወደሥራ መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን ዕቅዶቹን በየሩብ አመቱ ሲገመገሙ መቆየታቸው የቅንጅት አሠራሩን ውጤታማ እንዳደረገው ተገልጿል።

በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ ቅንጅታዊ ሥራ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ተቋማት የዕውቅና ምሥክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።