ቢሮው ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ድጋፍ አደረገ።

ቢሮው ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ድጋፍ አደረገ።

ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (አአ ሰፀአ ቢሮ)

*******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለመቅዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ድጋፍ አድርጓል ።

የቢሮው አማካሪ አቶ ኤልያስ መሐመድ ድጋፋን አስመልክተው እንደተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ላይ በርካታ ስራዎችን እንደሚሰራ ጠቅሠው ከዚህም ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባለው ተነሳሽነት ድጋፍ እንዳደረገና ቢሮው በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።

ስለ ማዕከሉ ገለጻ ያደረገው አቶ ፍቅሩ ቢኒያምሶ ሲሆን ማዕከሉ ከተመሰረተበት ወቅት አሁን እስከደረሰበት ድረስ በተለያዩ ልበ ደግ ማህበረሰቦች ገቢ እንደሚንቀሳቀስና በማዕከሉ ውስጥም ከ8500 በላይ የአዕምሮ ዕሙማንና አረጋውያን እንደሚገኙና በውስጡም ከህመማቸው በማገገም በእደ ጥበብና ውጤቶ። በቤተ መጽሐፍት ውስጥ በማገልገል ላይ እንሚገኙ ተናግረዋል።

ማዕከሉ የወጣቶች፣ የሴቶችና የወንዶች የመንከባከቢያ ክፍሎች እንደ የእድሜያቸው በበቂ ሁኔታ እንክብባቤ እንደሚደረግላቸውና በአሁኑ ጊዜም ማዕከሉ ግዙፍ ህንጻ እያሰራ እንደሚገኝም አቶ ፍቅሩ አብራርቷል ።

የቢሮው ብር 77,500 ገንዘብና አልባሳት ድጋፍ ደረገ ሲሆን ለተደረገለት ድጋፍም አመራሮችንና ሰራተኞችን አመስግነዋል ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የቢሮው አማካሪ አቶ ኤልያስ መሐመድን ጨምሮ ከቢሮው የተወከሉ ሰራተኞች ተገኝተዋል ።