የቢሮው የሀይማኖት እና የሰላም እሴት ግንባታ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቢሮው የሀይማኖት እና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል።

በከተማዋ የሚስተዋለውን ሰላምና መረጋጋት ለማስቀጠል የህብረተሰቡ ተሳትፎ ትልቅ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

ሰኔ 19/2017 ዓ.ም (አአ ሰፀአ ቢሮ)፦በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ በመድረኩ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት በከተማዋ የሰፈነውን ሰላምና መረጋጋት ለማስቀጠል የህብረተሰቡ ተሳትፎ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቅሰው የወንጀል ምጣኔን በመቀነስ አመርቂ ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።

አቶ ተስፋዬ አክለውም በሀይማኖታዊ በዓላት ወቅት በበጀት አመቱ ህብረተሰቡን በማወያየትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በማዘጋጀት ከጸጥታ አካላት፣ ከሀይማኖት አባቶች ጋር በቅንጅት በመስራት የነዋሪውን ሰላም ማረጋገጥ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔን ጨምሮ የዘርፉ የማዕከልና የክፍለ ከተማ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።