የስምንት ወራት ቅንጅታዊ ዕቅድ አፈፃፀም ሥራዎች ግምገማ
ቢሮው ከሸገር ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት ጋር የስምንት ወራት ቅንጅታዊ ዕቅድ አፈፃፀም ሥራዎችን ገመገሙ
መጋቢት 6/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተደር ቢሮ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ከሸገር ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት ጋር የስምንት ወራት ቅንጅታዊ ዕቅድ አፈፃፀም ሥራዎችን ገምግመዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት በልማትና መልካም አስተዳደር፤ሰላምና ደኅንነት ዙሪያ በቅንጅት የሰራነው ሥራ ውጤታማ ነበር፤በከተማችን ወንጀል ሰርተው ወደ ሸገር ከተማ የሚደበቁና ከሸገር ከተማም ወንጀል ሰርተው ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመምጣት የሚደበቁ እንዲሁም ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈፅሙ ህዝብን የሚያማርሩ ሰግብግብ ነጋዴዎች በሁለቱም ከተሞች በተሰራው ቅንጅታዊ ሥራ የወንጀል ምጠኔን መቀነስና ገበያን ማረጋጋት ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የፅንፍና የሽብር ኃሎች አዲስ አበባን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ያቀዱ ቢሆንም በሁለቱም ከተሞች በተደረገ ጠንካራ የፀጥታና ደህንነት ስምሪት የፀረ ሰላም ኃይሎችን ዓለማ በማክሸፍ የኃማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላት በሰላም ሊከበሩ ችለዋል ብለዋል፡፡
በበዓል ጊዜያት በቻ ሳይሆን በሁሉም የፀጥታ አዝማሚያ ላይ በሰላም ሰራዊትና በጋቸነ ሲርና አማካይነት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ለማድረግ የተሰሩ ቅንጅታዊ ስራዎች አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ነው ያሉት ክብርት የቢሮ ኃላፊዋ
አቶ ጉዮ ገልገሎ የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባ በበኩላቸው እንደተናገሩት ሰላም ሳይኖር ልማት ዕድገትና ብልፅግና የለምና ዘሬ በሰላም ጉዳይ ላይ እንወያያለን፡፡ ከተማችን ሸገር ከተመሰረተ ሁለት ዓመት ቢሆንም ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተሰርተው በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ ከነዚህ መካከል ለከተማችን ሰላም ትልቁን ስፍራ በመስጠት የሰራነው ስራ ተጠቃሽ ሲሆን ይህም ውጤት ብቻችን በሰራነው ሳይሆን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ያመጣነው ነው ብለዋል፡፡
የሥምንት ወራት ቅንጅታዊ ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ኃላፊ ሲሆኑ በሪፖርታቸውም፡-
• የኃማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው ማለፋቸው፤
• ዓለማቀፋዊ፤አህጉራዊና አገራዊ ጉባኤዎች፤ ኮንፈረንሶችና ስብሰባዎች በሰላም መጠናቀቃቸው፤
• የኑሮ ውድነትና የኢኮኖሚ አሻጥርን በመቆጣጠር ገበያ ማረጋጋት መቻሉ፤
• የተለያዩ የሽብርና ፀረ-ሰላም ኃይሎች፤ህገ-ወጥ የጦር መሳሪዎችን በጋራ በቁጥጥር ስራ ማዋላችን፤
• የወንጀል ምጣኔ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር 42% መቀነስ መቻሉ፤
የሁለቱ ከተሞች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች
• ከዋናው ዕቅድ የተቀዳና ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን ያገናዘበ የአንድ ወር ዕቅድ ማዘጋጀት፤
• የግንኙነት ጊዜ ካሁን ቀደም ከነበረው ባጠረ ጊዜ በየወሩ መገናኘትና ስራዎችን መገምገም፡፡
• ኬላዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ፤
• በነዳጅ ማደያዎች ላይ በቅንጅትና በተናበበ ሁኔታ ቁጥጥር ማድረግ፤
• ከዋናው ግብረሃል በተጨማሪ ቢሮዎች በዘርፋቸው እርበርስ ተሳስረዉ እንዲሰሩ ማድረግ ወዘተ ናቸው፡፡
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሊዲያ ግርማ ፤የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳር ቢሮ ም/ሃላፊዎች፤ ፅ/ቤት ሃላፊዎች፤በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዮ ገለገሎ፤ረዳት ኮሚሽነር ተሻለ ኦብሳ የሸገር ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ሃላፊ፤ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳርና የሸገር ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት የባለድርሻ አካላት ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡