የሶስተኛ ሩብ ዓመት የተቋማት ትስስር ሰነድ ዕቅ...

image description
image description
image description
- recent news   

የሶስተኛ ሩብ ዓመት የተቋማት ትስስር ሰነድ ዕቅድ አፈፃፀም

የቢሮው የቅንጅታዊ ሥራዎች ዉጤት የላቀ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለፀ

መጋቢት 4/2017 ዓ.ም( አዲስ አበባ)

******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮው የሶስተኛ ሩብ ዓመት የተቋማት ትስስር ሰነድ ዕቅድ አፈፃፀም በከንቲባ ፅ/ቤት በተቋቋመው የክትትልና ድጋፍ ቡድን ድጋፍና ክትትል እንደተደረገለት የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው ገልፀዋል፡፡

በክትትልና ድጋፉ ወቅት እንደተገለፀው በበጀት አመቱ በዕቅድ ከተያዙ 26 ዋና ዋና ተግባሮች መካከል ሃያ ስድስቱም መቶ ፐርሰንት መተግበራቸውን ቡድኑ አረጋግጧል ብለዋል፡፡

የድጋፍና ክትትል ቡድኑ የዕቅድ አፈፃፀሙ ከፍተኛ መሻሻልና የላቀ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀው፤ይህ ለሌሎችም ተቋሞች ጥሩ ተሞክሮ ሊሆን ስለሚችል ቢሰፋና በቀጣይ የዘጠኝ ወራት ሪፖርት እንዲጠመር አቅጣጫ በመስጠት የክትትልና ድጋፍ ስራዉ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡