ልምድ ልውውጥ

image description
- recent news   

ልምድ ልውውጥ

በዶ/ር እሸቱ የሱፍ የአማራ ክልል የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የተመራ የልዑካን ቡድን ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ።

          የካቲት 21/2017 ዓ.ም(አዲስ አበባ )
                   ******
የአማራ ክልል የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ  ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

ለልምድ ልውውጡ ለመጣው የልዑካን ቡድን ስለ አዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አደረጃጀትና አጠቃላይ የስራ ሂደት ማብራሪያ የሰጡት የቢሮው ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር እንደተናገሩት ቢሮው  በቅርብ ግዜ የተቋቋመ ቢሆንም ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው  አራት ዘርፍ (መረጃ, አደረጃጀት, ሰላም እሴት ግንባታ እና ኦፕሬሽን) ዘርፍ ያለውና 4ቱም በም/ቢሮ ሀላፊዎች የሚመራ እና በርካታ ዳሬክተሮች, ቡድን መሪዎችና ሰራተኞች አቅፎ በአዋጅ የተቋቋመ የከተማዋ ቁልፍ ቢሮ መሆኑን አንስተዋል። መዋቅሩም በክ/ከተማና ወረዳ ደረጃ ተዋቅር የከተማዋ ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሌት ተቀን እየተጋ ያለ ቢሮ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከተማችን  ከደረስበች የእድገትና የለውጥ ደረጃ መሰረት ያደረገ ሪፎርም ተሰርቶ መጠናቀቁንም አንስተዋል።

የፀጥታ ስራ በባህሪው አይን በመክደን እና በመክፈት መሀል ባለች ቅፅበት ውስጥ ተለዋዋጭ  ስለሆነ ሁል ጊዜም ዝግጁ ሆኖ ሌት ተቀን የሚሰራ አመራርና ሙያተኛ ቸፈጥሯል ብለዋል። ሁሌ በተንጠቀቅ መቆም ያስፈልጋል ብለዋል። 

ስለዚህም ቢሮው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማትና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተወጣጡ አደረጃጀቶች  ጋር በሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ላይ ሁልጊዜም በትብብር እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ ይሄም በመሆኑ ምክንያት የከተማችን ህዝብ የሰላሙ ባለቤት እየሆነ ነው መሆኑን የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት አብነትን በማንሳት አስረድተዋል። 

ቢሯች ከሌሎች ሀይሎች ጋር በመቀናጀት የፀጥታ ስጋት የሆኑ ህገ-ወጥ ተግባራትን ማለትም የኑሮ ውድነት የሚያባብሱ፣ትራንስፖርት እጥረት እንዲፈጠር የሚያደርጉ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈጥሩ፤  ለብልሹ አሰራር የተጋለጡና እና ሌሎች የጸጥታ ስጋት የሆኑ ጉዳዮች ላይ በመወያየት  ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይል ጎን እንዲቆም ከማድረጉም በላይ  ከሁሉም የጸጥታ ሀይሎች የተውጣጣ ግብረ-ሀይል ተቋቁሞ፤ የማስፈፀሚያ ዕቅድ እየተዘጋጀና እየተገመገመ እንደሚሄድም ገልጸፀውላቸዋል።

በዚህም በየጊዜውና አጋጣሚዎችን ተጠቅመው ከተማችንና ነዋሪዋን ለመረበሽ የሚያቅዱ, የሚሸርቡ የተለያዩ የውስጥና የውጪ የሽብርና የጽንፍ ሀይሎች በጥናት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ እርምጃ በጥምረት እንደሚወሰድ አንስተውላቸዋል።

ከተማ አስተዳዳሩ ቢሯችን ለማገዝ እና ለማበረታታት በበጀትም ሆነ በሀሳብ ስለሚረዳን ስራ ለመስራት የሚያስቸግረን ነገር የለም ብለዋል፡፡

አቶ ገብሬ ዳኘው የቢሮው አማካሪ በበኩላቸው አገልግሎት አሰጣጣችንን ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ማህበረሰቡ ምንም ልፋትና እንግልት ሳይገጥመው ቤቱ ሆኖ ጥቆማ እንዲሰጥና አገልግሎትም እንዲያገኝ  የመረጃ መረብ ለምቶ ወደ ተግባር መገባቱን  ገልጸዋል።

የልኡካን ቡድኖቹ የቢሮውን አደረጃጀትና የስራ ሂደት ትልቅ ተሞክሮ እንዳገኙበትና በክልላቸው ባሉ ከተሞችና ዞኖች ለመተግበር እንዳነሳሳቸው በአድናቆት አንስተዋል። በተለይ የጸጥታ አመራሩና ሰራተኛው ውስጣዊ መነሳሳት, ትጋትና ቅንጅት ለብዙዎች ልምድ የሚሆን ነው ብለዋል። የአዲሱ ጥናት ሰነድ, መመሪያዎች, ማንዋሎች, ቼክ ሊስቶችና ሌሎች መረጃዎች ለተሞክሮ ወስደዋል።

በመጨረሻም የልዑካን ቡድኑ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮን አደረጃጀትና አሰራር በመዘዋወር  ጎብኝቷል።