129ኛ የአድዋ ድል አከባበር
"ዓድዋ ያለምንም ልዩነት በተከፈለ መስዋትነት የተገኘ የጋራ ድል ነው"
ክብርት ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
የካቲት 20/2017 ዓም(አዲስ አበባ)
********
ዓድዋ ያለምንም ልዩነት፣ በአላማ ፅናትና አትንኩኝ ባይነት በተከፈለ መስዋትነት የተገኘ የጋራ ድል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በአራዳ ክፍለ ከተማ በተካሄደ መድረክ ላይ ገልፀዋል።
129ኛውን የአድዋ ድል በዓል " አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል'' በሚል መሪ ቃል በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተከብሯል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ መድረክ ላይ የተገኙት ክብርት ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለፁት፤ አድዋ ያለምንም ልዩነት፣ በአላማ ፅናትና አትንኩኝ ባይነት በተከፈለ መስዋት የተገኘ የጋራ ድል ነው ብለዋል።
ይህም ነፃ ሀገር ለማስቀጠል መሰረት የሆነና ለሌሎች አፍሪካዊያን ምልክትና መነሳሳትን የፈጠረ ብሎም የመላ ጥቁር ህዝቦች አንገትን ቀና ያደረገ ድል ነው ብለዋል።
የአሁኑ ትውልድም ከታሪክ በመማር በአንድነት ወቅቱ በሚጠይቀው የልማትና የሰላም ስራ የማስቀጠል ትልቅ ሀላፊነት እንዳለበት ገልፀዋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ መድረክ ላይ የአዲ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ፣አቶ ገታሁን አበራ የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፣ብርጋዴር ጀነራል ሁሉነገርሽ ይድረስ ከፈደራል መከላከያ ሚኒስቴር ፣የሃይማኖት አባቶች፣አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች፣የፈደራል ፖሊስ አመራር እና አባላት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራርና አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።