በከተማው ውስጥ ወንጀል ለመቀነስ፣የውስጥ ለውስጥ...

image description
image description
image description
image description
- recent news   

በከተማው ውስጥ ወንጀል ለመቀነስ፣የውስጥ ለውስጥ መንገዶችና የመንገድ ዳር መብራት ችግሮችን ለመፍታት በተዘጋጀ የማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ ።

በከተማው ውስጥ ወንጀል ለመቀነስ፣የውስጥ ለውስጥ መንገዶችና የመንገድ ዳር መብራት ችግሮችን ለመፍታት በተዘጋጀ የማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ ።

ታህሳስ 13/ 2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )

******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ውስጥ ወንጀል ለመቀነስ፣

የውስጥ ለውስጥ መንገዶችና የመንገድ ዳር መብራት ችግሮችን ለመፍታት በተዘጋጀው የማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ ውይይት አከሂዷል ።

በውይይቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንደገለፁት ከተማችን አዲስ አበባ ላይ አስተማማኝ ሰላም ማምጣት የተቻለው የከተማው ነዋሪ የጸጥታ ተባባሪና ተሳተፊ እንዲሆን በመደረጉና ከአዲስ አበባና ከፌደራል የፀጥታ ኃይሎች እንዲሁም ከሸገር ሲቲ አስተዳደር ገር በቅንጅት በመሥራታችን ነው

ብለዋል።

አሁንም በመዲናዋ ጨለማን ተገን አድርገው የሚፈፀሙ ስርቆቶች በተወሰነ ደረጃ መኖሩን በተደረጉ ጥናትና ግምገማዎች መለየቱን የገለፁት ኃላፊዋ፤ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 33 በመቶ የወንጀል ምጣኔ መቀነሱን ተናግረዋል።

በመሆኑም ጨለማን ተገን በማድረግየሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመቀነስ ማህበረሰቡንበማወያየት፤

ለወንጀል አጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት በቂ የመብራት ስርጭት እንዲሁም የመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታ በማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ወ/ሮ ሊዲያ ተናግረዋል።

ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ዋና ዋና የውስጥ ለውስጥ መንገድ መብራት የሌለባቸው ቦታዎች መለየታቸውንም የቢሮ ኃላፊዋ ገልፀዋል። ችግር ያለባቸው 174 አካባቢዎች ተለይተው መብራት እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

በውይይቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ፣አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ም/ሀላፊ፣

የአዲስ አበባ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አግልግሎት ሀላፊዎች፣ በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣የአዲስ አበባ መብራት አግልግሎት ባለስልጣን፣ ከህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ኮሚሽንና የሁሉም ክ/ከተማ የሰላምና ጸጥታ ፅ/ቤት ሀላፊዎች ተገኝተዋል።