የኮሪደር ልማት ስኬት እና የሰላም ፀጥታና ደህን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የኮሪደር ልማት ስኬት እና የሰላም ፀጥታና ደህንነት ዙሪያ ፓናል ውይይት ተካሄደ::

ቢሮው በ2017 ዓ.ም የኮሪደር ልማት ስኬት እና የሰላም ፀጥታና ደህንነት ዙሪያ ፓናል ውይይት ተካሄደ።

የካቲት 13/2017 ዓ.ም ( አዲስ አበባ )

******

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2017 ዓ.ም የኮሪደር ልማት ስኬት እና የሰላም ፀጥታና ደህንነት ዙሪያ ከ11ዱ ክ/ከተሞች የተወጣጡ የተለያዩ አደረጃጀቶች ተወካዮች ጋር ፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ

የዓለምን አይን የሳበ ልማት በከተማ ውስጥ እየተሰራ ያለው ሰላም ስላለ ነው።

በከተማው ውስጥ እየተከናወነ የሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማቶችና የከተማው የኮሪደር ስራ እየተፍጠነ በመሆኑ በዚህም ውስጥ ሁሉም የድርሻውን ሀላፊነት እየተወጣ ነው ያሉት ም/የቢሮ ኃላፊው ለዚህም የከተማው ነዋሪ ትልቁን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

በመድረኩም የሚሰራው ልማት ለአገር እና ለልጅ ልጅ የሚተርፍ ትልቅ ታርክ መሆኑን እና ገንዘብ ለማግኘት በሃሰተኛ መረጃዎች ህዝቡን የሚያንከራተቱ ግለሰቦች ከገንዘብ አገር ስለሚበልጥ ልብ ገዝተው እውነታውን ማጣራትና ትክክለኛው መረጃ ማድረስ እንዳለባቸው እንድሁም ሁሉም ዜጋ ባለው እውቀትና ጉልበት ልማቱን መደገፍ እንዳለበት መልዕክት የሚያስተላልፍ አጭር ትአትር በዥረቱ ትአትር ቡድን ቀርቦ አዝናኝና አስተማሪ መልዕክቶችን አስተላልፏል።

በመድረኩ ላይም የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደን ጨምሮ የአዲስ አበባ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አግልግሎት አባላት እና ከ11ዱ ክ/ከተሞች የተወጣጡ የተለያዩ አደረጃጀቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።