የቢሮው ለማዕከል ሰራተኞች ሙስና በተመለከተ የተሰጠ ስልጠና
የሙስና ፅንሰ ሀሳብና የመከላከያ ስልቶችን በተመለከተ ስልጠና ተሰጠ።
ጥር 29/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
*****
በስልጠናው ላይ የተሳተፉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የማዕከል ሰራተኞች ናቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰላም አምሳሉ እንዳሉት የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ሰልጣኞቹ ግንዛቤያቸውን ካዳበሩ በኃላ የሙስና መከላከያ ስልቶችን በመተግበር ከሙስና የፀዳ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮምሽን ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያ አቶ ደረጄ ግርማ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን ስለ ሙስና ፅንሰ ሀሳብ፣ልዩ ባህሪያት፣የሙስና ዓይነቶች፣ፖለቲካዊ ሙስና፣መንስኤዎችና
የሚያስከትሉ ጉዳቶችን አብራርተዋል።
በመጨረሻም ሰልጣኞቹ ላነሱዋቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራርያ ተሰጥቶበት ስልጠናው ተጠናቋል።