የ6ወር እክድ አፈጻጸም ግምገማ ከባለድርሻ ተቋማ...

image description
- recent news   

የ6ወር እክድ አፈጻጸም ግምገማ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር

የከተማዋን ሰላም እና ደህንነት ዘላቂ ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማን መፍጠር ተችሏል

 * የአዲስአበባ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ 

          ጥር 17/2017 ዓ.ም( አዲስ አበባ )

                    ******

የአዲስ አበባን ከተማን ሰላም እና ደህንነት ዘላቂ ለማድረግ በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ መፍጠር መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ ::

ቢሮዉ በጋራ ለመስራት ትስስር ከፈረሙ ባለድርሻ አካላት ጋር የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ነው ፡፡

የቢሮው ኃላፊዋ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አዲስ አበባን የደህንነት ስጋት የሌለባት ከተማ ለማድረግ እና ከተማዋን የሚመጥን ዘመናዊ የፀጥታ ተቋም ለመፍጠር በተሰሩ ስራዎች በርካታ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል። 

የከተማዋ ነዋሪዎችና እንግዶቿ ያለምንም የጸጥታ ስጋት ወጥተው እንዲገቡ ፣አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ ሰላም መረጋገጡንም ኃላፊዋ አመልክተዋል ::

በቅንጅት በተሰሩ ስራዎችም የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል።

የተቀናጁ የፀጥታ ስራዎች በመከናወናቸውም ከተማዋ ያከናወነቻቸው አህጉር አቀፍና አለም አቀፍ ጉባኤዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የአደባባይና የህዝብ በዓላትን ያለምንም የፀጥታ ችግር በድምቀት መከናወናቸውን አመልክተዋል ።

የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ  ባደረጉበት ንግግር
የግምገማው አላማ ጠንካራ ጎኖቻችን ለማስቀጠልና ክፍተቶቻችንን ደግሞ በቀሩት 6ወራት ውስጥ አሻሽለን ለመስራት መሆኑን ጠቁመው  የተለያዩ የአደባባይ በዓላትና ኩነቶች በሰላም ተከብረው ያለፉት በቅንጅታዊ ስራ፣ በህብረተሰቡ ተሳትፎና በአመራሩ ብስለት ነው  ካሉ በኃላ አሁንም የመረጠንን ህዝብ ሰለምና ደህንነት ለመጠበቅ  ብርድ ሳይገድበን ቀንና ሌሊት በታማኝነት እና በትጋት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

በመጨረሻም ባለፉት ስድስት ወራት በቅንጅታዊ አሰራር  የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ሴክተር ተቋማት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊና የዕለቱ የክብር ዕንግዳ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የክሪስታል ዋንጫ፣ዋንጫና የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።