የጥምቀት በዓል አከባበር በማስመልከት ከፀጥታ ሃ...

image description
- recent news   

የጥምቀት በዓል አከባበር በማስመልከት ከፀጥታ ሃይሎችና የተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር የተደረገ ውይይት

ቢሮው የጥምቀት በዓል አከባበር በማስመልከት ከፀጥታ ሃይሎችና የተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት አካሄደ።

    ጥር 08/2017 ዓ.ም ( አዲስ አበባ )

                   ********
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ   የጥምቀት በዓል አከባበርን በማስመልከት ከፀጥታ ሃይሎችና የተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ ላይም ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር እና የአ/አ/ከ/ህ/ፖሊስ አግልግሎት ረዳት ኮሚሽነር አይናለም በየነን ጨምሮ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት የክ/ከተማ አስተባባሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ የአደረጃ
ጀቶች የተወጣጡ ተወካዮች ተሳትፎዋል።

ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ ዓበዘርፉ ባለሙያ በወ/ሮ ሮማን በቀለ የቀረበ ሲሆን
ለፀጥታ  ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ቦታዎች ላይ ቀደም ተብሎ በተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ሁላቸውም የፀጥታ ሃይል አጋዥ በመሆን የድርሻቸውን መውጣት ይገባቸዋል ካሉ በኋላ በዓሉ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን በትኩረ መቆጣጠርና ፈጣን እርምጃ መውሰድ ከሁሉም ፀጥታ መዋቅር የሚጠበቅ መሆኑን ገልፀዋል።

መድረኩን የመሩት  ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ማህበረሰብ አቀፍ አግልግሎት ረዳት ኮሚሽነር አይናለም በየነ ሲሆኑ  አቶ ተስፋዬ በዚህ ጊዜ እንደተናገሩት በዓሉ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመሰገበ ነውና የተለያዩ ቱርስቶች የሚገኙበት ስለሆነ ባዓሉ  ዕሴቱን ጠብቆ  ይከበር  ዘንድ በተቀናጀና በተናበበ ሁኔታ ሃላፍነታችን በተገቢ መወጣት አለብን ብለዋል።