ለጥምቀት በዓል አከባባር የተሰጠው ኦረንቴሸን

image description
- recent news   

ለጥምቀት በዓል አከባባር የተሰጠው ኦረንቴሸን

የከተራና ጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በቢሮው በየደረጃው ላለው መዋቅር የተለያዪ ቴክኒካዊ ድጋፎችን ለማድረግ ለተቋቋመው
 ቡድን ኦረንቴሽን ተሰጠ።

        ጥር 8/ 2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )
                            **
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ መጭው የ2017ዓ.ም የጥምቀት በዓል በሰላም በደመቀና ባመረ መልኩ እንዲከበር የማዕከልና፣ የክ/ከተማ አስተባባሪዎች፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጥቷል።

በዓሉን በሰላም ለማክበር ቀደም ተብሎ የተሰሩና ያልተሰሩ በቀጣይ በቀሪ ቀናት በዓሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሊሰሩ የሚገባቸው ሥራዎች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ እንደገለፁት ሰሞኑን የከተማው ማህበረሰብ ሲወያይ  በዓሉ በሰላም ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ሰፊ ፍላጎት እንዳለውና መንግሦትና ባለድርሻ አካላት ፀጥታና ሰላሙን የማስጠበቅ ኃላፊነቱን መወጣት  እንደለበት ስላላሳሰበን ብቻ ሳይሆን ተግባርና ኃላፊነታችንም ስለሆነ  በሁሉም እንቅስቀሴዎች ላይ ችግሮች  ሲያጋጥሙ ይህ ቡድን በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር በመነጋገር በአፋጣኝ መፍታት  እንደሚገባውና ፈጣን የመረጃ ልውውጥ እንዲደረግም አሳስበዋል።