የጥምቀት በአል ቅድመ ዝግጅት

image description
- recent news   

የጥምቀት በአል ቅድመ ዝግጅት

የጥምቀት በዓል አንድነታችንን፣በህላችንንና መልካም ገፅታችንን ለዓለም ሕብረተሰብ ከፍ አድርገን ከምናሳይባቸው የአደባባይ በዓሎች አንዱ ስለሆነ ልንጠብቀው ይገባል ተባለ

      ጥር  06/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

                        ***** **

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብክት ጋር በመተባበር ከደብር አስተዳዳሪዎችና የፀሐፊዎች ጋር የጥምቀት በዓል አከባበርን በማስመልከት የማጠቃለያ ውይይት አድርገዋል።
      
የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  በዚህ ወቅት እንደተናገሩት የዘንድሮ የጥምቀት በዓልን ለየት የሚያደርገው ከዚህ ቀደምት ሲነሱ የነበሩ የታቦታት ማደሪያ ቦታዎች ችግሮች በኮሪደር ልማቱ ምክንያት ምቹና ሳቢ በሆነ መልኩ መሠራታቸው ነው ብለዋል።

የጥምቀት በዓል አንድነታችንን፣በህላችንንና መልካም ገፅታችንን ለዓለም ሕብረተሰብ ከፍ አድርገን ከምናሳይበቸው  የአደባባይ በዓሎች
መካከል አንዱ ስለሆነ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ፍፁም ሰላማዊ በሆኖ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ሚናውን እንዲወጣ አሳስበለሁ ብለዋል።

የዛሬው የማጠቃለያ መድረክ ዋና ዓላማ በዓሉ ታላቅ የአደባባይ በዓል በመሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ሰላምን የሚያደፈርሱ ጉዳዮች ላይ በቀጣይ ቀሪ ቀናቶች ውስጥ መስተካከል እንዲችሉ ምክክር የሚደረግበት መድረክ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብክት ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ማህምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ፣የመወያያ ሰነድ ሲያቀርቡ፣በዓሉ ሰላማዊም መንፈሳዊም እንዲሆን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ  ኮምሽነር ጌቱ አርጋው  በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት የጥምቀት ዓለም አቀፍ የአደባባይ በዓል እንደመሆኑ መጠን በዓሉን ለመታደም በርካታ ቱሪስቶች ወደ ሀገራችን ስለሚገቡ በተለየ ትኩረት መሥራት እንደሚያ
ስፈልግ ተናግረዋል።

ኮምሽነር ጌቱ አክለውም የኮሚሽኑ የፀጥታ ስራዎች አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ በማለቱ ከምንም በላይ ቅድሚያ በመስጠት በዓሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ፣የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮምሽነር ጌቱ አርጋዉ፣የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ማህምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ፣ሌሎችም የቢሮው የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች
ተገኝተዋል።