የ2017 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የ2017 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና የጥምቀት በዓል አከባበር ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ውይይት እየተደረገ ነው።

የ2017 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና የጥምቀት በዓል አከባበር ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ውይይት እየተደረገ ነው።

ጥር 02/2017 (አዲስ አበባ)

****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ዕሴት ግንባታና የሃይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት የ6ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና የመጪውን የጥምቀት በዓል አከባበር ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉ አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ዕሴት ግንባታና የሃይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ ውይይቱን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ ከተከናወኑ ክንውኖች መካከል ጠንካራ አፈፃፀም የተመዘገበባቸውን በጥንካሬ በማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በፍጥነት በማረም በቀሪ ስድስት ወራት ዉስጥ የላቀ የአፈፃፀም ዉጤት ማሰመዝገብ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

አቶ ተስፋዬ አክለውም ከፊታችን የሚከበረው የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው ይህ ዘርፍ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም የሚመለከተው አካል የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት ብለዋል።

የሰላም ዕሴት ግንባታና የሃይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ የስልጠና ባለሙያ የሆኑት አቶ ኤሊያስ ቀጄላ የበገት ዓመቱን የሥድስት ወራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ባለፉት ወራት ስድስት ወራት ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መከበራቸው ከጠንካራ የግብ ስኬቶች አንዱ ሲሁን አልፎ አልፎ ከታችኛው መዋቅር ጀምሮ የተሰሩ ስራዎችን ለቅሞ በየእርከኑ ላለው አካል ወቅቱንና ጥራቱን የጠበቀ ሪፖርት ያለመላክ እንደ ክፍተት የተስተዋሉ ችግሮች መሆቸውን ጠቅሰዋል፡፡

መጪውን የጥምቀት በዓል አከባበር በተመለከተ ቢሮው ቀጣይ ሳምንት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የሃይማኖት ተቋማት ጋር ተከታታይ ውይይት እንደሚያደርግ ጠቅሰው ሌሎች ቀሪ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ከወዲሁ መጨረስ አለብን ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔና የማዕከል የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡