የቢሯችን ጠቅላላ ካውንስሉ የመጀመሪያው ግማሽ ዓ...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቢሯችን ጠቅላላ ካውንስሉ የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ገመገመ

የቢሯችን ጠቅላላ ካውንስሉ የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ገመገመ

ጥር 01/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ )

*******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮና ተጠሪ ተቋሙ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የጠቅላላ ካውንስል የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት ገምግሟል።

በጠቅላላ ካውንስሉ ላይ የሁለቱም ተቋማት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ጥልቅ ግምገማ ተካሂዷል።

በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት የጸጥታ መዋቅቱ በጥምር ሀይል በመገምገምና ጥብቅ ስምሪት በመስጠት እንዲሁም ህዝቡ የሰላም ባለቤት በማድረግ የወንጀል ምጣኔ እንዲቀንስ ተደርጓል።

በከተማችን የተካሄዱ አለም አቀፍና አህጉራዊ ኮንፈረንሶችና ሴሚናሮች ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲያልፋ ብርቱ ስራ መሰራቱን የግምገማው ተሳታፊዎች አንስተዋል።

በበጀት አመቱ ግማሽ አመት በከተማችን የተካሄዱ ባህላዊና ሃይማኖታዊ የአደባባይ በአላት ህዝቡ የሰላም ባለቤት በማድረግ በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ መደረጉን በግምገማው ተነስቷል።

ህገ-ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ እንዲቀንስ፣ ህገ ወጥ የጎዳና ንግዶች ለማስቀረት፣አዋኪ ድርጊቶች ላይ እርምጃ የመውሰድ, የኮሪደር ልማት ያለአንዳች የጸጥታ ችግር እንዲከናወን በቅንጅት እንደተሰራ በሪፓርት ቀርቦ ተገምግሟል።

የግምገማ መድረኩን የመሩት የቢሮ ሀላፊያች ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለጹት በበጀት አመቱ ግማሸ አመት ህዝባዊና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላትና ሌሎችም የአደባባይ ፕሮግራሞች በሰላም እንዲከበሩ ከተማ አቀፍ ንቅናቄ በመፍጠር ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከከተማችን ህዝብና ከፀጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅትና በትብብር በ7/24 በመስራታችን ያለፀጥታ ችግር እንዲከበሩ ማድረግ መቻሉ አንስተዋል።

በከተማችን የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥና የደንብ ጥሰቶች እንዲቀንሱ በሁለቱም ተቋማት መልካም አፈፃፀም ማስመዝገባቸውን አንስተዋል።

የአገልግሎት አሰጣጥን የተቀላጠፈ ለማድረግ ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር, አገልግሎቶች በቴክኖሎጅ ለማስደገፍ, የበጀት አጠቃቀምና የፋይይናንስ አስተዳደር, የሪፎርም ስራዎች ለማሳለጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን አንስተዋል።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት በግማሽ አመቱ በሁለቱም ተቋማት አመርቂ ውጤቶች እንደተመዘገቡ በማውሳት ለቀጣይ ስራዎቻችን ስኬት ስንቅ መሆኑን አንስተዋል። አያይዘውም ተቋም ግንባታ, ሌብነትና ብልሹ አሰራር ከአስተሳሰብ ጀምሮ ታግሎ ማረም, ቅንጅታዊ ስራዎችን ማጠናከርና አገልግሎት አሰጣጥ ማቀላጠፍ በቀጣይ አተኩረን መስራት እንዳለብን አንስተዋል።

በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊያችን በቀጣይ በልዩ ትኩረት መሰራት ያለባቸው ዝርዝር ተግባራት ላይ መመሪያ ሰጥቷል።

አንደኛውና የመጀመሪያው በሁለቱም ተቋማት ተቋም ለመገንባት የተጀመሩ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ መደረግ እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተቷል። በአመለካከት የተቀየረ, ሌብነትና ብልሹ አሰራር የሚጠየፍ, በሚሰራው ስራ ውጤታማ የሆነና ተወዳዳሪና ብቁ አመራርና ሰራተኛ መፍጠርና መገንባት ላይ በትኩረት እንዲሰራ መመሪያ ሰጥቷል። ለዚህም ከተማችን የደረሰችበት የእድገት ደረጃ የሚሸከም አደረጃጀት የመፍጠር ስራ በልዩ ትኩረት በየወቅቱ በስትራቴጂክ አመራሩ እየተመራ በፍጥነት እንዲተገበር አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ሁለተኛው ከወረዳ ጀምሮ በተቋሞቻችን የሚታዩ የሌብነትና ብልሹ አሰራር አስተሳሰቦችና ድርጊቶች የተደራጀ የስነ ምግባር ስርጸት ስራ የመስራትና ተጠያቂነት የማስፈን ስራ በልዩ ትኩረት በየወቅቱ የግምገማና የክትትል አካል ተደርጎ መሰራት እንዳለበት መመሪያ ሰጥተዋል።

ሶስተኛ የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አኳያ የከተማችን ሰላም የማፅናት ጥረትን ማስቀጠል፣ ህዝቡ የሰላም ባለቤት የማድረግ ስራችን የበለጠ የማጠናከር ስራችን, የፅንፈኞችና የሽብር ኃይሎችን እንቅስቃሴ መከታተል, የደንብ ጥሰቶችን የማረም ስራችን, የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ማጠናከር, የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ መፍታት፣ የጥምቀት በአል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ በቂ ዝግጅት መደረግ እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተው አቅጣጫ አስቀምጧል።

በግምገማ መድረኩ የሁለቱም ተቋም አመራሮችና ዳሬክተሮች ተገኝቷል።