በውስጥ ኦዲት መመሪያና አሰራር ዙሪያ የግንዛቤ...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በውስጥ ኦዲት መመሪያና አሰራር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በውስጥ ኦዲት መመሪያና አሰራር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ታህሳስ 24/ 2017 ዓ/ም

******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ለማዕከል ሰራተኞች በውስጥ ኦዲት አሰራር ዙሪ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

የስልጠናው ዓላማ ለውስጥ ኦዲትም ትኩረት በመስጠት የመስሪያ ቤቱ የውስጥ ቁጥጥር እንዲጠናከር በማድረግ በኦዲት ግኝት ላይ ለሚፈጠረው ስህተት እርምጃ በማስወሰድ ተጠያቂነት እንደሚኖረው ለማስቻል በማሰብ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ወ/ሮ አለም ታደገ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ የማህበራዊና አስተዳደራዊ የኦዲት ቡድን መሪ ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት የውስጥ ኦዲት ሥራ በመስሪያ ቤቱ የስራ እንቅስቃሴ ውስጥ ተጨማሪ እሴት እንዲፈጠር የተቀረጸ ነጻና ገለልተኛ የህግ ማረጋገጫ ምስክር አግልግሎት በመስሪያ ቤቱ የተዘረጋለት፤ ስጋት ያለባቸውን የሰራ ዘርፎች በመለየት የአስተዳደር የውስጥ ቁጥጥር እና አሰራር ሂደት ለመገምገም የሚያስችል ስርዓት ነው ብለዋል፡፡

በስነ-ምግባር የታነፀ የፋይናንስ አሰራር ሥርዓት ስራ ላይ በመዋል የመ/ቤቱን ዓላማ ከግብ ለማድረስ እንዲቻል በመሆኑ በውስጥ ኦዲት አሰራር ላይ የሚከናወኑና የማይከናወኑ ተግባራት እንዲሁም የሚስተዋሉ ችግሮችን በተመለከተ ገለፃ ሰጥተዋል።