ለሁለተኛ ዙር አዲስ ምልምል እጩ የሰላም ሰራዊ...

image description
- recent news   

ለሁለተኛ ዙር አዲስ ምልምል እጩ የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና መስጠት ተጀመረ ።

ለሁለተኛ ዙር  አዲስ ምልምል እጩ የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሀሳብና የተግባር  ስልጠና መስጠት ተጀመረ ።

        ታህሳስ 22/ 2017 (አዲስ አበባ )
                      ******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማው ሰላም ከምንግዜውም በላይ አስተማማኝ ለማድረግ ሁለተኛ ዙር  አዲስ ምልምል እጩ የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሀሳብና የተግባር  ስልጠና መሰጠት ጀምሯል፡፡

አዲስ ዕጩ የሰላም ሰራዊት አባላትን በመመልመል በዛሬው ዕለት በሁሉም ክ/ከተሞች የስልጠና  የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊዎች የክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች፤የክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች የክፍለ ከተማ ዕጩ የሰላም ሰራዊት አባላት፣እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
 
በመድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ም/ቢሮ ሀላፊዎች፤ የክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች፤የክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች  እንደተናገሩት ከፀጥታ መዋቀሩ ጋር በመቀናጀት የከተማችን ሰላምና ደህንነት  በማረጋገጥ የጸጥታ ስጋትና ወንጀል እንዲቀንስ በማድረግ የተለያዩ ሃይማኖታዊ እና የአደባባይ የሁነቶች ያላምንም የፀጥታ ችግር ተከብረው እንዲያልፍ በማድረግ ዉስጥ የሰላም ሰራዊቱ ሚና እጅግ የላቀ እንደነበር ጠቅሰዋል። 

ሃላፊዎቹ አክለውም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም ቀጣይነት ለማረጋገጥ ህብረተሰቡ ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም፤ የሰላም ሰራዊቱን  በሰው ኃይል፤በሥነ ልቦናና በተሻለ የፀጥታ ጥበቃ ግንዛቤ ደረጃ ላይ ለማድረስ 2ኛው ዙር ዕጩ የሰላም ሰራዊት አባላት መመልመል፤ማሰልጠንና ማሰማራት ማስፈለጉን ጠቅሰው አሁንም ከፊታችን ባሉ ጥቂት ቀናት የጥምቀት በዓልና የአፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ስለሚካሄድ ነባሩና አዲስ የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በተለመደው ተነሳሽነት የከተማውን ሰላም የማፅናት ተልዕኳቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

ስልጠናው በ 11 ማዕከላት ለ11ሺ አዲስ ምልምል እጩ የሰላም ሰራዊት አባላት የሚሰጥ ሲሆን "የሰላም ምንነትና ዘመኑን የዋጀ ሀገር ወዳድነት" በሚል ርዕስ የንድፈ ሃሳብና  የመስክ ወታደራዊ ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን ስልጠናውን እንደጨረሱ ከ10 ቀናት በኃላ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት የምርቃ መረሃ ግብሩ እንደሚከናወን ለማወቅ ተቸሏል፡፡