የመንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
በመንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን መመሪያ አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ።
ታህሳስ 21/ 2017 (አዲስ አበባ )
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ለማዕከል ሠራተኞች በመንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን መመሪያ አዋጅ 56/2010 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል።
በግንዛቤ ማስጨበጫው ስልጠና ማስጀመሪ ላይ በመገኝት መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው አማካሪ አቶ ተሻለ አክሊሉ እንዳሉት ሰራተኞች ህግና መመሪያን በበለጠ አውቀው ስራዎችን በተገቢው መንገድ ለማከናወን እንዲረዳቸው፤
የህግ ጥሰት እንኳን ሲፈጸም አውቀው ለተጠያቂነት ዝግጁ እንዲሆኑ ለማድረግ ይረዳል በማለት ተናገረዋል።
ስልጠናው የሰጡት አቶ ደጉ የኔ ነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ስርጸት አቃቢ ህግ ባለሙያ ሲሆኑ ሠራተኞች መብትና ግዴታችን መደረግ ስላለባቸውና ስለሌለበት ጉዳዮች በማወቅ ህግና ስርዓትን በተከተለ መልኩ መስራት ይጠበቅባቸዋል ካሉ በኃላ ሰራተኞች ህግን ከተላለፉ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ጠቅሰው ፍትህ የማግኘት መብትም አላቸው ብሏል።